አልፈራም


Monday, September 18, 2017

ያንድ ጉዞ ቲኬት

ያንድ ጉዞ ቲኬት
ልመለስ የለበት … ምንም ቢናፍቁ … ምንም ባይስማማ፣ አንድ”ዜ ከሄዱ … ወደ ሰፊው ሐገር … ወደሞት ከተማ፡፡ የደርሶ መልስ ትኬት … አይቆረጥ ከቶ፣ አንዴ መሄድ ብቻ … በሰሌን ተከቶ፣ እዛ ሞት ከተማ … ችሎት ተዘርግቶ፣ ቅን ፍርድ ይፈረዳል … ቲኬታችን ታይቶ፡፡ብልጥ መሳይ ሞኞች … የደርሶ መልስ ቲኬት … ተሳስተው ቢቆርጡ፣በመመለሻቸው … ለዳግም ሞት ጭልፊት … ላሞራው ተሰጡ፡፡ ያንድ ጉዞ ትኬት … ስሟ ነው ንስሐ … ስሟ ነው ጥምቀት፣ ያንድ ጉዞ ቲኬት ስሟ ነው ምስጋና … ስሟ ነው ስግደት፡፡ እለት እለት … ሁሉ በእርሷ እንቀደስ፤ የእሳት ሰረገላው … እስኪወስደን ድረስ፡፡