ግጥሞች አጫጭር ልብወለዶች ወጎችና ትዝታዎች
የኔ እግር ይኼ ነው ! ይህን የኔን እግር ... ተራራ ቁልቁለት ... ሄጄበት ሳበቃ፣ ና ልጠብህ ቢለኝ ... ትሁት እረኛዬ ... የነፍሴ ጠበቃ ፣ የ ጫማዬን ክሮች ... ለመፍታት ከበደኝ ... እንዲያይ የኔን ዱካ፣ስንት የረገጥኩበት ... በቅዱስ እጆቹ ... ሊታጠብ ነው ለካ፣ እርሱ ካላጠበኝ ... የኔ መለቃለቅ ... መቼም አያስመካ !!
Comments
Post a Comment