የልቤ ዓምድ
በድንጋይ
ምሰሶ፣ … በሰማይ ስር ቆመህ፣
ዓለምን
ከግርጌህ፣ … አምላክን ከፊትህ አድርገህ፣
ሉቃስ
ሆይ አሳየህ፣ የነፍስን ከፍታ፣
በሥጋ
መሸነፍ፣ በዓለም ሳትረታ፡፡
አንተ
ከላይ ቆመህ፣ …
የውሽንፍር ብዛት ፣ በጸሐይ ንዳዱ፣
መቼም አልገታህም ..
ከማይነጥፍ ምስጋና ፤ የለሊቱ ብርዱ፡፡
እኔ
ግን በምድር፣ በሺህ ሩጫ
መሃል፣
ንፋስ እየገፋው፣ ልቤን እንደቅጠል፣
ስባክን እየዋልኩ ፣ ተኝቼ አድራለሁ፣
ጌታን ለማመስገን ፣ ግዜም አላገኘሁ፡፡
እስቲ ደገፍ ልበል ፣
ከቤተስኪአን ሄጄ፣ አምዱን ልደገፈው፣
እንዳይናወጥም ፣ ልቤን ቢያረጋጋው፣
“እምነቴ” ይጽናልኝ ፣ አማልደኝ ቅዱሱ፣
አይሳበኝ አይጣለኝ ፣ አሰሱ ገሰሱ፡፡
አንተ
ከፍ ብለህ፣ ...
በሰማይ ዙፋን ፊት፣ ባምላክ ዘንድ ያለኸው፣
ከሀሳብ
ግርግር...
ከዚህ ዓለም ውክቢያ ነጻ የወጣኸው፡፡
እንዳመልጠው እርዳኝ ... አማልደኝ አደራ፣
የልቤ ምሰሶ .. ዳግም እንዲሰራ፣
እግሬ
መሬት ይርገጥ፣ ልቤም ካንተ ጋራ፣
ሰማዩን
ልመልከት ፣
ምድሩን ሳልፈራ ፣
ቃሉ በልቤ ላይ ፣
ሁሌም እንዲዘራ፣
ሰላሳና ስልሳ ፣ መቶም እንዳፈራ፡፡
"ዓምዳዊው"፣ ጸሎትህ ትኑር ከኛ ጋራ፡፡
ከፍታው
አይራቀኝ፣ መንፈሴ አይውረድ፣
በፍቅሩ
ታስሬ፣ ልሂድ ባንተ መንገድ።
Comments
Post a Comment