የመላእክት አለቃ ቆሟል ከፊታችን !!
ብርሃን ባለበት በሰማዩ ስፍራ፣
ቅዱስ ገብርኤል ቆሟል ብርሃን እያበራ፣
ካልባስጥሮስ ክንፎች እጅግ የሚልቁ፣
በቀንና በሌት ከአምላክ መልእክት ይዘው ሰውን የሚያነቁ፣
ከአምላክ ፊት ቆሞ ትዕዛዝ የሚቀበል እኛን የሚያረጋ፣
ሰማያዊ ምስጢር ለ እኛ እንዲገለጥ በምልጃው የተጋ ፣
ገብርኤል እኮ ነው ባለንበት እንቁም ብሎ ያረጋጋ ።
ለእናታችን ማርያም...
ጸጋን የሞላብሽ ብሎ ያበሰራት ፣
ደስ ይበለሽ ብሎ ሰላምታ የሰጣት፣
የትንሳኤን ብስራት ...
ከባዶ መቃብር ደጃፉ ላይ ቆሞ፣
ያበሰረ እርሱ ነው ከፍጥረታት ቀድሞ፣
የጠፉ ነብሳትን ወደብርሃን መሪ፣
የተስፋ ምልክት የሰላም አብሳሪ ፣
በ እርሱ ፊት ስንሆን ክንፉ ሲጋርደን ፣
ገብርኤል ገብርኤል ገብርኤል እንላለን ፣
ሰማያዊ ብርሃን ባንተ ውስጥ ስላየን፣
በጸሎት በመዝሙር እናከብርሃለን።
ከአምላክ ፊት ስለሆንክ አማልደን አደራ፣
በስጋም በነፍስም ከቶ እንዳንፈራ ፣
እንደ አባቶቻችን ፍቅራችንን አብዛው ፣
ለዓለም በሙሉ መረጋጋት ይሁን ወከባ ለናጠው፣
በ እምነት እንድንጸና አንተ አረጋጋን መስቀሉን እንያዝ ፣
ጽኑ እያልክ አንቃን ወደፊት እንጓዝ ።
Comments
Post a Comment